በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የኮሮናቫይረሱ ዴልታ ዝርያ እጅግ ተላላፊ ከሆኑት የመተንፈሻ የሚያጠቁ ቫይረሶች መካከል አንዱ ነው" የሲዲሲ ዳይሬክተር


የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል /ሲዲሲ/ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼል ዋለንስኪ
የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል /ሲዲሲ/ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼል ዋለንስኪ

ኮቪድ-19 ከሚያስከትሉት ኮሮናቫይረሶች መካከል አንዱ ዝርያ የሆነው ዴልታው እስካሁን ካወቅናቸው ከፍተኛ ፍጥነት ተላላፊ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ ቫይረሶች መካከል አንዱ ነው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል /ሲዲሲ/ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼል ዋለንስኪ ተናገሩ።

እኔም በሙያዬ ባሳለፍኳቸው ሃያ ዓመታት ካጋጠሙኝ እጅግ ተላላፊዎች ቫይረሶች መካከል አንዱ ነው ሲሉም አክለዋል።

ትናንት ሃሙስ ዶክተር ዋሌንስኪ እና ሌሎችም ባለስልጣናት ህዝቡ የኮቪድ-19 ክትባቱን በመከተብ ራሱን ከዚህ እጅግ ተላላፊ ቫይረስ ራሱን እንዲጠብቅ እና ቫይረሱ እንዳይስፋፋ እንዲያደርግ ተማጽነዋል።

በሌላ በኩል ቻይና የዓለም የጤና ድርጅት ኮሮናቫይረስ የተስፋፋው ከዉሃን ቤተ ሙከራዋ አፈትልኮ ይሆን እንደሆን ክትትሉን ለመቀጠል መፈለጉ እንዳላስደሰታት አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG