በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 ክትባት


ዩናይትድ ስቴትስ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባትን ለመፍጠር ለማምረትና በዓለም ዙሪያ እኩል ለማከፈፋል የተወጠነው ዓለምቀፍ ዕቅድ የመሪነቱን ሚና የያዘው የዓለም የጤና ድርጅት ስለሆነ አልሳተፍበትም ስትል አስታወቀች።

የዓለም የጤና ድርጅት የወረርሽኞች ዝግጁነት ጥምረት እና ለድሃ ሃገሮች ህጻናት ክትባት ለማዳረስ በሚልና መሊንዳ ጌትስ የተቋቋመው ድርጅት የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽነት ላይ የሚሰራ የጋራ መርሃ ግብር ዘርግተዋል፤ አንድ መቶ ሰባ ሃገሮች በእቅዱ ለመሳተፍ እየተነጋገሩ ናቸው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የዓለም የጤና ድርጅትን የወረርሽኙን ጉዳይ በትክክል አልያዘም፣ ስርጭቱ ለመነጨባት ለቻይናም ያዳላል በሚል ወንጅለው ባለፈው ሃምሌ ሃገራቸውን ከድርጅቱ ማስወጣታቸው ይታወሳል።

የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጀድ ዲር ባወጡት መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ ወረርሽኙን ለማሸነፍ ከዓለም አቀፍ አጋሮችዋ ጋር መስራቷን ትቀጥላለች፤ ይሁን እንጂ በዓለም የጤና ድርጅት እና በቻይና ተጽዕኖ በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ግን አንገደብም ብለዋል።

XS
SM
MD
LG