በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት


ፎቶ ፋይል፦ የዓለምቀፍ የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም
ፎቶ ፋይል፦ የዓለምቀፍ የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም

የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተሻለ ፍትሃዊነት መዳረስ እንደሚገባው የዓለምቀፍ የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም አሳሰቡ። ባለጠጎቹ ሃገሮች ለደሆቹ ክትባቱን ማካፈል አለባቸው ብለዋል።

የዓለምቀፍ የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ዛሬ በድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በድሆች ሃገሮች የጤና ሰራተኞችና አረጋውያን ሳይከተቡ፣ የባለጠጎቹ ሃገሮች በጤና ይዞታቸውም በዕድሜቸውም ያልገፉ ዜጎች መከተባቸው ልክ አይደለም ብለዋል።

ዕቅጩን ልናገር ያሉት ቴድሮስ አድኃኖም ከዓለም ድሃ ሃገሮች በአንዷ እስካሁን የተከተበው ሃያ አምስት ሰው ብቻ ነው፤ ቢያንስ አርባ ዘጠኝ በሚሆኑ ከበርቴ ሃገሮች ግን እስካሁን ሰላሳ ዘጠኝ ሚሊዮን ሰው ተከትቧል ሲሉ አነጻጽረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደሩን ተረክበው በመጀመሪያዎቹ አንድ መቶ ቀናት ውስጥ አንድ መቶ ሚሊዮን ሰዎች ክትባቱን ያገኛሉ ሲሉ ያወጡት ግዙፍ ዕቅድ በደምብ አድርጎ ሊከናወን የሚችል ነው ሲሉ የሃገሪቱ ዋናው የተላላፊ በሽታዎች አዋቂ ዶክተር አንተኒ ፋውቺ ተናገሩ።

XS
SM
MD
LG