ዋሺንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር 4,675,628 መድረሱንና በበሽታው ሳቢያ ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች ቁጥር ደግሞ 154,944 መድረሱንየጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል መረጃ አስታውቋል።
በዓለም ዙሪያ የቫይረሱ ተጋላጮች ቁጥር 18,117,821 መሆኑ ለህልፈት የተዳረጉት 690,181 መድረሱን ነው መረጃው የሚያሳየው፤ ዩናይትድ ስቴትስ በቫይረሱ ተጋላጮች ብዛት በዓለም ዙሪያ ከተመዘገበው አንድ አራተኛ ገደማውን ይዛለች።
ዋይት ሃውስና የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ዲሞክራቶች ለብዙ ሚሊዮን ሥራ አጦች ድጋፍ የሚውል የፌዴራል መንግሥት ወጪ በሚጨምረው እቅድ ላይ ዛሬም ድርድራቸውን ቀጥለዋል።
በወረርሽኙ ሳቢያ ከሥራቸው ለተፈናቀሉ ሰዎች በየሳምንቱ ሲሰጥ የነበረው ስድስት መቶ ዶላር ባለፈው ሳምንት ማብቃቱ ይታወቃል።