በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዩናይትድ ስቴትስ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተረጋገጠው የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር ወደ 3ሚሊዮን እየተቃረበ ነው፤

የሀገሪቱ ዋናው የተላላፊ በሽታዎች አዋቂው ዶክተር አንተኒ ፋውቺ "በተለያዩ አካባቢዎች በወቅቱ የሚታየው የሞት መጠን መቀነሱን አይታችሁ መዘናጋት ውስጥ እንዳትገቡ ሲሉ አሜሪካውያንን አስጠንቅቀዋል።

የብሄራዊ የአለርጂና የተላላፊ በሽታዎች ኢንስቲቱት ዳይሬክተሪ ፋውቺ ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጡት ትናንት ከአላባማ ሴኔተር ደግ ጆንስ ጋር በፊስቡክ ለውይይት ቀርበው ነው።

የሞት መጠኑ መቀነሱን አይቶ እፎይ ማለቱ አጉል ነው፥ ምክንያቱም ይሄ ቫይረስ የሚደርሳቸው ሌሎች ብዙ ከባድ ጠንቆች አሉና ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኮቪድ-19 ሳቢያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ዛሬ አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ሽህ አራት መቶ ሃምሳ ሰባት መድረሱን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩንቨርስቲ መረጃ ያመለክታል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ግን የሞት መጠኑ በአስር እጥፍ አሽቆልቁሏል ብለው በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

XS
SM
MD
LG