በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዩናይትድ ስቴትስ


ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ
ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ

በዩናይትድ ስቴትስ በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር ከ130ሺህ ማለፉን ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የወረርሽኙ መረጃ ማዕከል የተገኘው መረጃ አሳይቷል።

በኮቪድ-19 ሳቢያ በሞቱት ሰዎች ብዛት ብቻ ሳይሆን በተረጋገጡ የቫይረሱ ተግላጮች ቁጥርም ዩናይትድ ስቴትስ አሁንም ዓለምን መምራቷን ቀጥላለች። በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር 2.9ሚሊዮን በላይ ደርሷል።

በዚህ የአውሮፓውያን ሃምሌ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ውስጥ በቀን ከ50ሺህ በላይ ቫይረሱ የያዛቸው ሰዎች ተመዝግበዋል፤ በርካታ ክፍለ ግዛቶች በቀን ውስጥ ከምንጊዜውም ብዛት ያላቸው ተጠቂዎች እየተገኙ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ሁኔታው የሀገሪቱ የተላላፊ በሽታዎች ግንባር ቀደሙ አዋቂ ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ በወረርሽኙ የመጀመሪያ ማዕበል አሁንም እስከጉልበታችን እንደተነከርን ነን ሲሉ የሰጠቱን ማስጠንቀቂያ አጠናክሮታል።

ወርርሽኙ ከከፋባቸው ክፍለ ግዛቶች አንዷ የሆናቸው ቴክሳስ በአንድ ቀን ከተመዘገቡት ትልቁ የሆነውን 8ሺህ 7መቶ ተጋላጮች ማግኘቷን ገልጻለች።

XS
SM
MD
LG