ዋሺንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች፣ ለህልፈት በተዳረጉትም ከዓለም ትልቁን አሃዝ እንደያዘች ነች።
በአሁኑ ጊዜ የቫይረሱ ተጋላጮች ቁጥር ከ2.3ሚሊዮን ያለፈ ሲሆን በበሽታው ሳቢያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 121,228 ደርሷል።
አሪዞና፣ ካሊፎርኒያ፣ አርካንሳ፣ ደቡብና ሰሜን በአሁኑ ወቅት ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መዛመት ከጀመረበት ጊዜ ሁሉ ቁጥሩ የበለጠ የተያዥችም ሆነ ታመው ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየታየ ነው።
ፕሬዚዳንት ትረምፕ የኮቪድ-19 ምርመራ ጋብ እንዲል ባለሥልጣኖቻቸውን ቢያሳስቡም ከፍተኛው የሃገሪቱ የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ኢክስፐርቱ ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ ትናንት ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት በሰጡት የምስክርነት ቃል ምርመራው ይጨምራል እንጂ አይቀነስም ብለዋል።