በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በድሬዳዋ ተዘግተው የነበሩት የአሸዋና ታይዋን ገበያዎች ሥራ ጀመሩ


ከኮሮናቫይረስ ስጋት ጋር በተያያዘ በድሬዳዋ አስተዳደር ለ17 ቀናት ተዘግተው የነበሩት የአሸዋና ታይዋን ገበያዎች ዳግም ሥራ ጀመሩ። በአንፃሩ ጫት ተራ ተብሎ የሚታወቀው ዋናው የጫት መገበያያ ስፍራ ተዘግቶ በሦስት የከተማዋ ሜዳማ ቦታዎች የጫት ግብይቱ እንዲካሄድ አስተዳደሩ ወስኗል። ተዘግተው የነበሩ አብዛኞቹ ሆቴሎችና ቡናቤቶችም እንዲከፈቱ ተፈቅዷል።

ከድሬዳዋ መውጣትና መግባት ተከልክለው የነበሩ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችም በግማሽ የመጫን አቅማቸው እንዲሰሩ ተፈቅዶላቸዋል። በሀረሪ ክልልም ተመሳሳይ የማሻሻያ ዕርምጃዎች እየተወሰዱ ሲሆን የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ግን በእነኚህ ማሻሻያዎች ኅብረተሰቡ ሊዘናጋ አይገባም ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በድሬዳዋ ተዘግተው የነበሩት የአሸዋና ታይዋን ገበያዎች ሥራ ጀመሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:39 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG