በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በደቡብ አፍሪካ


ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር፣ 300,000 በደረሰበት በአሁኑ ወቅት፣ የሃገሪቱ አየር መንገድ፣ መልካም ዜና ማሰማቱ ተገለፀ። በመንገዳገድ ላይ የነበረው አየር መንገድ፣ ከሃገሪቱ መንግሥት የገንዘብ ድጎማ እንደሚያገኝ ተገልጿል።

በኮቪድ-19 ምክንያት የተዘጉ ድንበሮችና የአየር በረራ መስመሮች፣ ቀስ በቀስ እየተከፈቱ ባሉበት በአሁኑ ውቅት፣ ሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶችም፣ ድጎማ እያገኙ መሆናቸው ታውቋል።

በአጠቃላይ የአየር መጓጓዣ ሁኔታው የጨለም ነው ተብሏል። ኮሮናቫይረስ በዓለምቀፍ ደረጃ፣ የአየር በረራ ኢንዱስትሪን ክፉኛ የጎዳ ሲሆን፣ በበርካታ የአፍሪካ አየር መንገዶች ላይ ግን፣ ለሞት ሊያበቃ የሚችል ያህል ጉዳት እንዳደረሰባቸው ታውቋል።

ቫይረሱ በአፍሪካ ዙሪያ ባሉት የአየር በረራ ኢንዱስትሪዎች ላይ ያደረሰው ጉዳት፣ በቢልዮኖች ዶላሮች የሚቆጠር ገቢን እንደሚያሳጣና በሚልዮኖች የሚቆጠሩ የሥራ ቦታዎችን ሊያከስም እንደሚችል ጠበብት ይተነብያሉ።

ወደ አፍሪቃ የሚደረገው የጉብኝት ፍሰትና ከአህጉሪቱ ወደ ውጭ የሚላኩት የሮዝ አበቦችና የአትክልት ምርቶችም፣ ትልቅ ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል ጠበብቱ ይናገራሉ።

XS
SM
MD
LG