በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በደቡብ አፍሪካ


ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የስድስተኛና የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ወደትምህርት ቤት ተመልሰዋል። ከሦስት ወራት በፊት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከገባ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትምህርት ቤት መግባታቸው እንደሆነም ተዘግቧል።

በትምህርት ቤቶቹ የዕጅ ማጽጃዎች የተዘጋጁ ቢሆንም አንዳንድ ወላጆች ግንልጆችን የጥንቃቄ መንገዶችን ተግባራዊ ማስደረግ ይከብዳል የሚል ስጋት እያሰሙ ናቸው። የሃገሪቱ የዜና ማሰራጫዎችም ይህን የተማሪዎች ወላጆች ስጋት ይጋራሉ።

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሰባተኛ ክፍልና ተመራቂ ተማሪዎች ከአንድ ቀን በፊት ትምህርት ቤት መመለሳቸውን ተከትሎ ከ2ሺህ በላይ መምህራን እና ከ1ሺህ በላይ ተማሪዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል።

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እስካሁን የተረጋገጠው የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቁጥር ከ2መቶ ሺህ አልፏል ፤ ከ3ሺህ በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል።

XS
SM
MD
LG