ዋሺንግተን ዲሲ —
“እርግጥ ነው ኮቪድ- 19 በመጀመሪያ ደረጃ ትልቅ የጤና ቀውስ ነው። ሌላ ደግሞ በሰው ልጅ የረጅም ጊዜ ታሪኩ ካየነው ደግሞ ምንም እንኳን ቫይረሱም ሆነ የሚያስከትለው በሽታ አዲስ ቢሆኑም፣ የሰው ልጅ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለሚያስከትሉ ትላልቅ ክስተቶች ሲጋለጥ ግን የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም። እንዴት ለእነዚህ ነገሮች መዘጋጀት እንዳለበትና እንዴትም አድርጎ አብሯቸው መኖር እንደሚችል በሂደት ያለፈበት ነው። “ ዶ/ር ተፈሪ አባተ አደም በዩናይትድ ስቴትሱ Yale ዩኒቨርሲቲ የስነ-ሰብ ተመራማሪ።
“ዘመን የጠገቡ ቤት ያፈራቸው” መላዎች አዲስ ወረርሽኝ ለመመከት እንደምን ለጥቅም ሊውሉ ይችላሉ?
ሳይንስና ባሕል የሚገናኙበት መስመር ይኖር ይሆን?
እስካሁን ፈዋሽ መድሃኒትም ሆነ የመከላከያ ክትባት ላልተገኘለት ወረርሽኝ ቀድሞ መሰል ወረርሽኞች በተነሱ ጊዜ የበሽታውን መዛመት ለማገድ ለጥቅም የዋሉ ዘዴዎች ዛሬ የሚጠኑበትንና ለጥቅም የሚውሉበትን ብልሃት እንመርምር ከሚሉ ባለሞያ ጋር የተደረገ ቆይታ ነው።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።