በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዴልታ ቫይረስ ተጋላጮች ቁጥር መጨመር በዩናይትድ ስቴትስ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የባይደን አስተዳደር የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ አሜሪካውያን በሙሉ ዴልታ የሚባለውን በፍጥነት ተላላፊ ቫይረስ ለመከላከል ተጨማሪ ማጠናከሪ ክትባት እንዲከተቡ በዚሁ ሳምንት ውስጥ ማሳሰቢያ ማውጣት ሊጀምር መሆኑን ዘገባዎች አመለከቱ።

በዴልታው ቫይረስ ሳቢያ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የቫይረሱ አዲስ ተጋላጮች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው።

ባለፈው ሳምንት የፌዴራሉ መንግሥት የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር (ኤፍዲ ኤ)እና የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል(ሲዲሲ) የሰውነት የተፈጥሮ መከላከያቸው የተዳከመ የሆኑ ሰዎች ድጋሚ እንዲከተቡ ምክረ ሃሳብ አውጥተው እንደነበር ይታወሳል።

በሌላ ዜና ኒውዚላንድዋ ትልቋ ከተማ ኦክላንድ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጠ አንድ ግለሰብ መገኘቱን ተከትሎ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን በመላ ሃገሪቱ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀን ከቤት ያለመውጣት ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

የሃምሳ ዘጠኝ ዓመቱ የቫይረሱ አዲስ ተያዝ ወሌሊላ አካባቢ ሄዶ እንደነበር ነው የተገለጸው ሆኖም ቫይረሱ ከየት እንዳገኘው ግን አልታወቀም።

በሀገሪቱ በስድስት ወር ውስጥ በቫይረሱ መያዙ የታውቀ የመጀመሪያ መሆኑ ነው። ግለሰቡ የተጓዘበት አካባቢ እና ኦክላንድ ከተማ ለሰባት ቀን እንዲዘጉ ጠቅላይ ሚኒስተሯ ወስነዋል።

XS
SM
MD
LG