በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዓለም


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዓለም የጤና ድርጅት ካለፈው ታህሳስ ወር አንስቶ በዓለም ደረጃ ካለው፣ 10ሚሊዮን የኮቪድ-19 በሽተኞች ቁጥር 60 ከመቶው በያዝነው ሰኔ ወር ላይ እንደተከሰተ ገልጿል።

ይህም የቫይረሱ መዛመት እየከፋ መሄዱንና ፍጥነቱም እየቀነሰ አለመሆልኑን እንደሚያስይ የጤናው ድርጅት አስገንዝቧል።

በየቀኑ ከ160ሺህ በላይ አዲስ የቫይረሱ በሽተኞች እየተመዘግቡ መሆናቸውን፣ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገልጸዋል። ሀገሮች ዓለምቀፉን ወረርሽኝ ለመታጋል፣ ማድረግ ያለባቸውን ተግባሮች ዘርዝረዋል።

“እያንዳንዱ በኮሮና ቫይረስ የሚጠረጠር ሰውን ለይቶ ማቆየት፣ ምርመራ ማካሄድናማከም፣ ከቫይረሱ በሽተኞች ጋር የተነካኩ ሰዎችን ፈልጎ ማግኘት እንደሚያስፈልግ፣ የጤና ሰራተኞችን ማሰልጠንና ለሥራቸው የሚያስፈልጉ ቁሶችን ማቅረብ እንዲሁም ማኅበረሰቦች ራሳቸውን እንዲከላከሉ ማስተማር ግድ እንደሚል፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም መክረዋል።

የአፍና የአፍንጫ መሽፈኛ ጭምብል ማድረግ ከበሽታው ያድናል ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ፣ ኮቪድ-19ኝን የመከላከሉን ተግባር በተሟላ መልኩ የማይፈጽሙ ሃገሮች ከባድ ሁኔታ ይጠብቃቸዋል በማለት አስጠንቅቀዋል።

XS
SM
MD
LG