በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መመሪያ በኢትዮጵያ


የጤና ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሣ
የጤና ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሣ

ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መመሪያ ላይ ሰሞኑን የተደረገው ማሻሻያ ዐዋጁንና እና እየተደረገ ያለውን ቁጥጥር ለማላላት ያለመ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የተደረገው መሻሻያ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ያስገባ እንጂ መላላትን የሚያመለክት አለመሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

ሰሞኑን በተሻሻለው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መመሪያ ከውጭ ሃገራት የሚመጡ ሰዎች ከለይቶ ማቆያ የሚወጡበት ጊዜ ከ14 ቀን ወደ 7 ቀን ዝቅ ብሏል።

ተኝቶ መታከም የማያስፈልጋቸውና እመች ሁኔታ ያላቸው በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች በቤታቸው እንዲቆዩም ይፈቅዳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኮቪድ-19 የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መመሪያ በኢትዮጵያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:01 0:00


XS
SM
MD
LG