በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞደርና ፍይዘርና ባዮንቴክን ከሰሰ


የሞድርና ክትባት
የሞድርና ክትባት

የኮቪድ-19 መድሃኒት አምራች የሆነው ሞደርና ተፎካካሪው በሆኑት ፋይዘር እና የጀርመን መድሃኒት አምራች የሆነውን ባዮንቴክ ላይ “ቴክኖሎጂዬን ኮርጀው የራሳቸውን መድሃኒት ለመስራት ተጠቅመዋል” በሚል ክስ መስርቷል።

በአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ መሰረት ሞደርና ዛሬ እንዳስታውቀው የፋይዘርና የባዮንቴክ የኮቪድ-19 ክትባቶች የተሰሩበት መንገድ፣ ከዓመታት በፊት ያስመዘገበው የፈጠራ ባለቤትነትን የሚጋፋ ነው።

ሞደርና ክሱን በአሜሪካ ፌዴራል ፍ/ቤትና እና በጀርመን በሚገኝ ፍ/ቤት አስገብቷል።

የፋይዘር ቃል አቀባይ “የክሱ ቅጂ አልደረሰንም” በሚል አስተያየት ከመስጠት መቆጠባቸውን የኤፒ ዘገባ አመልክቷል።

ሞደርናም ሆን ፋይዘር፤ ሰዎች የኮሮና በሽታን እንዲከላከሉ የሚያስችላቸውን ክትባቶች የሚሰሩት ኤምአርኤንኤ የተሰኘውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ነው።

የሞደርና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ስቴፋን ቦንሴል በጽሁፍ በተዘጋጀ መግለጫቸው እንዳሉት፣ ቴክኖሎጂውን በመጀመሪያ የፈጠረው ሞደርና መሆኑንና፣ ለዚህም በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንዳወጣበት ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG