በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህንድ በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ከ70ሺህ በላይ አዲስ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች ተገኙ


ፎቶ ፋይል፦ ኒው ዴልሂ /ህንድ/
ፎቶ ፋይል፦ ኒው ዴልሂ /ህንድ/

ህንድ ባለፈው የሃያ አራት ሰዓት ጊዜ 70,421 አዲስ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች መገኘታቸውን ተናገረች። ይህ አሃዝ የጤና ሚኒስቴሩ እንዳለው ባለፉት ሰባ አራት ቀናት ውስጥ በአንድ ቀን ሲመዘገበው ከቆየው ሁሉ ዝቅተኛው እንደሆነ ተገልጿል።

በዩናይትድ ስቴትስ ጃንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል መሰረት ህንድ እስካሁን በጠቅላላው በሀገሪቱ ያሉት የቫይረሱ ተጋላጮች ቁጥር 29 ነጥብ አምስት ሚሊዮን እንደገባ ማስታወቋን ገልጾ ሆኖም የጤና ጥበቃ ባለሥልጣናት ቁጥሩ ሊበልጥ እንደሚችል ማመልከታቸውን አክሎ ገልጿል።

ከህንድ የሚበልጥ ቁጥር ያላት ዩናይትድ ስቴትስ ብቻ ስትሆን በአሁኑ ወቅት አሃዙ 33 ነጥብ 5 ሚሊዮን ገብቋል። ሦስተኛውን ብዛት የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች ያገኘችው ብራዚል ደግሞ 17 ነጥብ 4 ሚሊዮን እንዳሉ የሆፕኪንሱ መረጃ ይጠቁማል።

XS
SM
MD
LG