በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዩናይትድ ስቴትስ


በዩናይትድ ስቴትስ በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥርከ2መቶ ሺህ አልፏል።

ይህንኑ ምክንያት በማድረግ ትናንት በጎ ፈቃደኞች በመዲናዋ ዋሺንግተን በሚገኘው የዋሺንግተን ሃውልት ሥር ሃያ ሺህ ትናንሽ የዩናይትድ ስቴትስ ባንዲራዎችን ዙሪያውን ተክለዋል። እያንዳንዱ ባንዲራ በበሽታው ምክንያት የሞቱ አሥር ሰዎች መታሰቢያ እንደሚሆን ተገልጿል።

በተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች በስፍራው በተከናወነው የጸሎት ሥነ ስርዓት ላይ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ንግግር አድርገዋል።

ይሄ ሁሉ ሰው ለሞት እንዳይዳረግ መከላከል ይቻል ነበር ያሉት አፈ ጉባኤ ናናሲ ፐሎሲ አሁንም የሰው ሞት እንዳይቀጥል ሳይንሱን እንከተል ሲሉ ተማጽነዋል።

በዛሬው ዕለተም በዩናይትድ ስቴትስ በኮቪድ-19 የሞቱት ሰዎች ቁጥር 200,890 መድረሱን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል መረጃ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG