በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዩናይትድ ስቴትስ


ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ትናንት 47ሺህ የኮሮናቫይረስ በሽተኞች ተገኝተዋል። ዓለማቀፉወርርሽኝ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ በአንድ ቀን ውስጥ ይህን ያክል ብዛት ያላቸው በሽተኞችን ስታስመዝግብ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ብዙዎቹ በሽተኞች ያሉት በአሪዞናና ቴክሳስ ክፍላተ-ግዛት ሲሆን፣ በካሊፎርኒያ፣ ፍሎሪዳ፣ ጆርጂያና ደቡብ ካሮላይናም ብዙ የቫይረሱ በሽተኞች እንዳሉ ተዝግቧል።

በዩንይትድ ስቴትስ ዙሪያ የኮቪድ-19 በከፍተኛ ደረጃ የመዛመቱን ሁኔታ ለመቆጣጠር፣ እርምጃ ካልተወሰደ ባስተቀር፣ አሁን የታየው የቫይረሱ በሽተኞች ብዛት፣ በእጥፍጨምሮ በቀን 100ሺህ ሊደርስ ይችላል ሲሉ፣ የብሄራዊ የአለርጂና የተላላፊ በሽታዎች ተቋምሃላፊ አንተኒ ፋውቺ አስጠንቅቀዋል።

“በአሁኑ ወቅት የቫይረሱን መዛት ለመቆጠጠር እንዳልቻልን ግልጽ ነው” ብለዋል። የበዙ የቫይረሱ በሽተኞች ባሉባቸው ከፍላተ-ግዛት ላይ የሚያተኩረው ኮሜቴ፣ መላ ሃገሪቱን አደጋ ልይ እየጣለ ነው በማለትም፣ ፋውቺ በአፅንዖት አስጠንቅቀዋል።

አንጋፋው የተላላፊ ባሽታዎች ምሁር ፋውቺ ይህን ያሉት፣ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ፊት ቀርበው፣ ስለቫይረሱ መዛመት ባስረዱበት ወቅት ነው።

ከዓለም የበዙ የኮቪድ-19 በሽተኞች ያሏት ዩናይትድ ስቴትስ ስትሆን፣ በዓለም ደረጃ 2.6 ሚልዮን የቫይረሱ በሽተኞች እንዳሉ ታውቋል። 127,000 የሚሆኑት ደግሞ በሞት ተለይተዋል።

XS
SM
MD
LG