በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ዕለታዊ የኮቪድ አስራ ዘጠኝ ይዞታ መረጃ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረጉ 5500 የላብራቶሪ ምርመራዎች ውስጥ አንድ መቶሃያ ዘጠኝ (129) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራየተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1934 ደርሷል፡፡

ተጠቂዎቹ ከ1 ዓመት እስከ 90 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 75 ወንዶች እና 54 ሴቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥም 124 ኢትዮጵያውያን እና፣ ቀሪዎቹ የደቡብ አፍሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ የሱዳን፣ የአሜሪካ እና የኤርትራ ዜጎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስተር ዛሬ ከሰዓት በፌስቡክ ገጹ አማካኝነት ይፋ አድርጓል፡፡

110 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 10 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 6 ከሶማሌ፣ 5 ከትግራይ፣ 5 ከኦሮሚያ፣ 1 ከሃራሪ እና 1 ሰው ከጋምቤላ ናቸው፡፡በሌላበኩል ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአንድ የ80 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊ የ አዲስ አበባ ነዋሪህይወት አልፏል። ሟቿ ወደ ሆስፒታል ለሌላ ህክምና በመጡ በአንድ ሰዓት ወስጥ ህይወታቸውሊያልፍ ችሏል። በአስክሬን ምርመራም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችንቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሃያ (20) ደርሷል፡፡

በተያያዘ በትላንትናው ዕለት (2 ከትግራይ ክልል፣ 6 ከአፋር ክልል፣ 1 ከሶማሊ ክልል እና 10 ከአዲስአበባ) በጥቅሉ 19 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፡፡

XS
SM
MD
LG