ዋሺንግተን ዲሲ —
የወባ መድኃኒትን ለኮቪድ 19 ሕክምና ማዋል ይቻላል? “ምን ይቀርብናል?” ይላሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ። “የለም፤ ፍቱን ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለንም” የሚሉም አሉ _ ከሕክምናውና ከምርምሩ ዓለም ቤተሰቦች መካከል ያሉ።
ክትባቱን ለማድረስ የሚማስኑ፤ መድኃኒት ከባሕላዊውም ከዘመናዊውም አድርገን እንቀምማለን የሚሉም ጥቂት አይደሉም፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ።
ከሁሉም ወገኖች እየተነሣ ያለውን ንግግር ሰሎሞን አባተ በተከታዩ ቅንብር አካትቷል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ