በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዓለም


የኢንግላንድና የዌልስ መጠጥ ቤቶች
የኢንግላንድና የዌልስ መጠጥ ቤቶች

ብሪታንያ ውስጥ እየተባባሰ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ሥርጭት ለመቆጣጠር ጠበቅ ያሉ ደንቦች ሥራ ላይ እየዋሉ ናቸው። የኢንግላንድና የዌልስ መጠጥ ቤቶች ከትናንት ሃሙስ ጀምሮ ደንበኞቻቸው በጊዜ አስተናግደው እየዘጉ ናቸው።

የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስር ቦሪስ ጆንሰን ባፀኑት የእንቅስቃሴ ክልከላ ከትናንት ማታ አራት ሰዓት ጀምሮ ምግብና መጠጥ ቤቶች እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተሰጥተዋል።

ስኮትላንድ ዛሬ ዕገዳውን ተግባራዊ አድርጋለች፤ ሰሜን አይርላንድ እያሰበችበት ናት። ፈረንሳይ ውስጥ ደግሞ ካለፈው ሰኔ ወር ወዲህ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ታመው ጽኑ ህክምና ክፍል የሚገቡ ህሙማን ቁጥር ትናንት ሃሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ሽህ ማለፉን የጤና ባለሥልጣናት ገለጹ።

ኔዘርላንድ ውስጥም ትናንት ብቻ 2544 አዲስ የኮሮናቫይረስ ተያዦች የተመዘገቡ ሲሆን እስካሁን በአንድ ቀን ከተገኙት የቫይረሱ አዲስ ተጋላጮች አሃዝ ትልቁ መሆኑን የጤና ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል።

እስራዔል ውስጥም የኮሮናቫይረስ ሥርጭቱ መባባሱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሃገሪቱ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ቀደሙት ሙሉ የእንቅስቃሴ ክልከላ ትዕዛዞች እንደምትመለስ አስታውቀዋል።

ለሁለት ሳምንታት በሚቆየው ዕገዳ ትምህር ቤቶች እና የመዝናኛ ሥፍራዎች እንዲሁም አብዛኞች የንግድ ድርጅቶች ይዘጋሉ፤ ምግብ ቤቶች ለበላተኛ ማድረስ እንጂ አስገብተው ማስተናገድ አይችሉም። ነዋሪዎች ለሥራ ወይም መድሃኒት ለመግዛት ካልሆነ በስተቀር ከመኖሪያቸው ርቀው መውጣት ተከልክሏል።

XS
SM
MD
LG