በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዓለም ዙሪያ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በዓለም ዙሪያ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ቁጥር 5,618,829 መድረሱን የጆንስ ሃፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ ጠቆመ። በበሽታው እስካሁን ለህልፈት የተዳረጉት ደግሞ ከ351ሺህ አሻቅቧል። በዩናይትድ ስቴትስ የቫይረሱ ተጠቂ ብዛት ከ1ሚሊዮን 684ሺህ ያለፈ ሲሆን የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 100ሺህ እየተቃረበ ነው።

ደቡብ ኮሪያ በአርባ ዘጠኝ ቀናት ውስጥ ከፍተኛው የሆነውን አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር መመዝገቧን ዛሬ ይፋ አድርጋለች። ዋና ከተማዋ ሶል አቅራቢያ አርባ ሰዎች መገኘታቸውን ነው ይፋ ያደረገችው።

በአሁኑ ጊዜ ብራዚል በኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ብዛት ዩናይትድ ስቴትስን እየተከተለች ሲሆን ትናንት ብቻ 1ሺህ 39 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

ህንድ ዛሬ ስድስት ሺህ አዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች መዝግባለች አጠቃላይ ቁጥር ከ150ሺህ አልፏል።

XS
SM
MD
LG