በምዕራቡ ዓለም የመጀመሪያው የኮረናቫይረስ መከሰቱ በምርመራ የተረጋገጠበት ጣሊያን ወረርሽኙ የተከሰተበትን አንደኛ ዓመት አሰበች።
የዛሬ አንድ ዓመት ነበር ጣሊያን ከእስያ ውጭ የኮረናቫይረስ መከሰቱ ሲረጋገጥ የመጀመሪያዋ አገር የሆነችው። ባለፈው ዓመት የካቲት 12፣ 2012 ዓም የኮዶኞ ከተማ ነዋሪ የሆነው 38 ዓመቱ ጎልማሳ ለኮረናቫይረስ መጋለጡ ሲረጋገጥ የመጀመሪያው ጣሊያናዊ የሆነው። ከሰዓታት በኋላም በቬኔቶ ክፍለ ግዛቷ የቮ ከተማ ነዋሪ የ77 ዓመቱ አረጋዊ በዚሁ ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉ ተዘገበ።
ብዙም ሳይቆይ መላውን ዓለም በፍጥነት ያዳረሰው ወረሽኝ ዛሬ ከ111 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ተጠቂ ሲያደርግ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሕልፈት ዳርጓል።
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ እና የጣሊያኑ ፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ የትላንቱን የኮረናቫይረስ ወረሽኝ አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ሐኪሞች፣ ነርሶች እና ሌሎች የህክምና አገልግሎት ሰጭዎች የሚከበሩበት ብሄራዊ የጤና ባለሞያዎች ቀንነት በመሰየም አስበውታል፡፡
“ግለኝነትን እና ራስ ወዳድነትን የሚከላከል ክትባት” ባሉት ሥራ “ቁርጠኝነታቸውን ያስመሰከሩትን የጤና ባለሞያዎች በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ያለውን ሌሎችን የመርዳት እና ራስን የመስጠት ትክክለኛ ፍላጎት እና ተፈጥሮ ያንጸባረቀ ነው።” ብለውታል። ፕሬዝዳት ማትሬላ’ም በበኩላቸው የህክምና ባለሞያዎቹ ያሳዩት የጀግንነት ምግባር "ወረርሽኙ ወደ ማይቀለበስ አደጋ እንዳይሸጋገር" ረድቷል” ሲሉ አወድሰዋል፡፡
የተለያዩ ሃገሮች ሕዝባቸውን የጸረ-COVID 19 ክትባት ለመከተብ ጥድፊያ ላይ ባሉበት ባሁኑ ወቅት የኒው ዮርክ ከተማ መጠኑ ከ1000 ያላለፈ ክትባት ብቻ እንደቀራት ተገለጠ። የከንቲባው ቢል ደ ብላዚዮ ቃል አቀባይ አቬሪ ኮኸን ትላንት በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት "መላክ የነበረበት ክትባት ፈጥኖ ባለመድረሱ አጠቃላዩን የክትባት ሂደት ሙሉ በሙሉ ለማቆም ተገደናል” ብለዋል።
መጠኑ 6 ሚሊዮን የሚደርስ ክትባት ክትባት ጨምሮ የተለያዩ ሸቀጦችን ከቦታ ማጓጓዝ ያሰናከለው በዩናይድ ስቴትስ የተለያዩ ግዛቶች የወረደው እጅግ በረዶ እና ከፍተኛ አውሎ ነፋስ አዘል ዝናም ነው ፡፡ የክረምቱ የአየር ሁኔታም እንዲሁ ቁጥራቸው 2 ሺህ በሚደርሱ የክትባት ጣቢያዎች የኃይል መቆራረጥ ማስከተሉም ተዘግቧል፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ - ሮም —