በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 እና ስፖርታዊ ውድድሮች በዩናይትድ ስቴትስ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

በዩናይትድ ስቴትስ በዘልማድ በበልግ ወይም በቀጣዮቹ ወራት ይካሄዱ የነበሩ ስፖርታዊ ክንውኖች፣ በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ እንዲሸጋገሩ ተወሰነ። ዓለምቀፉ ወረርሽኝ በስፖርቱ ዓለምም ጫና ማስደሩ ሲጣቆም ሁለት ዓበይት የዩናይትድ ስቴትስ የኮሌጆች አትሌቲክ ጉባኤዎች፣ የኳስ ጨዋታዎች እንዲራዘሙ ውሳኔ ተላልፏል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ አትሌቶቹ ጠንካራና ወጣቶች በመሆናቸው፣ ቫይረሱን የመታገል አቅም አላቸው በማለት፣ ጨዋታው በተለመደው ጊዜ እንዲካሄድ ሲገፉ ቆይተዋል።

ብሄራዊ የባስኬት ቦልና ብሄራዊ የሆኪ ሊጎች፣ በወረሽኙ ምክንያት የውድድር ጨዋታቸውን፣ በተማከሉ ቦታዎች ለማካሄድ ተገደዋል።

በርካታ የቤዝቦል ሊግ ተጫዋቾች፣ በኮቪድ-19 ስለተያዙ፣ ብዙ የውድድሮች ጊዜን ለማስተላለፍ ግድ ሆኖባቸዋል።

በሌላ በኩል 100 ሚልዮን የሚሆኑ የኮቪድ-19 ክትባት ዶዞች ተመርተው እንዲቀርቡ፣ በሀገሪቱ ፈዴራል መንግሥትና በአንድ የዩናይትድ ስቴትስ የባዪቴክኖሎጂ ኩባንያ መካከል ስምምነት መደረጉን፣ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ትናንት አስታውቀዋል።

ክትባቱን ለማምረት የተዋዋለው ሞደርና ኩባንያ፣ በክትባቱ መድሃኒት ላይ የፍተሻ ሙከራ እያካሄደ መሆኑ ሲዘገብ ቆይቷል። ኩባንያው የክትባቱን መድሃኒት የሠራው፣ ከብሄራዊ የአለርጂና የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ጋር በመተባበር ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሦስት የክትባት መደሃኒቶች፣ በሰዎች ላይ የመጨረሻው ደረጃ ሙከራ፣ እየተደርገባቸው መሆኑ ተዘግቧል።

የክትባቱ መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ከፀደቀ በኋላ፣ 100 ሚሊዮን ዶዞችን በፍጥነት ለማምረት ዝግጁ ነን። ከዚያም ወድያውኑ 500 ሚሊዮን ክትባቶች ይመርታሉ ሲሉ፣ ፕሬዚዳንት ትረምፕ በዋይት ኃውስ በተደረገ፣ ጋዜጣዊ ጉባኤ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG