በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደሴ ማረሚያ ቤት ውስጥ የህግ ታራሚዎች ለኮሮናቫይረስ ተጋለጡ


በደሴ ማረሚያ ቤት በተደረገ የኮቪድ-19 ምርመራ 10 ህግ ታራሚዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋገጠ፡፡

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ለኮሮናቫይረስ ህክምና ለመስጠት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ አገልግሎት መስጠቱን አስታወቀ፡፡ በሁለቱም ዞኖች ውስጥ የሚስተዋለው መዘናጋት ቫይረሱ በአሳሳቢ ደረጃ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡

ደሴ ከተማ ጤና መምሪያ ኃላፊ አብዱልሃሚድ ይመር ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ እንደገለጹት ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ተቋማት ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው፡፡ ከነዚህም በከተማዋ የሚገኘው የደሴ ማረሚያ ቤት አንዱ እንደሆነ ጠቁመው ሰሞኑን በታራሚዎች ላይ በተደረገ ምርመራ 10 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጦ ወደ ቦሩ ሜዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለህክምና ተልከዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ደሴ ማረሚያ ቤት ውስጥ የህግ ታራሚዎች ለኮሮናቫይረስ ተጋለጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:18 0:00


XS
SM
MD
LG