ትግራይ —
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት አርሶ አደሮች ገበያ በማጣት የችግሩ ገፈት ቀማሽ አድርጓቸዋል። በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ለቪኦኤ አስተያየት የሰጡ በመስኖ ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች ያመረቱት ምርት ለኮሮና መከላከል ተብሎ በወጣው ህግ ወደ ገበያ ለማቅረብ ባለመቻላቸው ምርታቸውን በማሳ ላይ ተበላሽቶ እንደቀረ ተናግረዋል።
የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ በጉዳዩ ተጠይቆ የአርሶ አደሩ ምርት በሕብረት ሥራ ማሕበራትና ሕጋዊ ነጋዴዎች በኩል ወደ ገበያ እንዲቀርብ እየተሰራ ነው ሲል አስታውቋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።