ዋሺንግተን ዲሲ —
ሩዋንዳ የኮሮናቫይረስ መዛመትን ለመገደብ፣ አዳዲስ እገዳዎችን ዛሬ ታስታውቃለች። ከቅርብ ቀናት በፊት የመኪኖች በመላ ሀገሪቱ መንቀሳቀስን፣ ገደቦችን የመላላት እቅድ እንደነበራት ታውቋል።
ሩዋንዳ ውሳኔውን የቀለበሰችው፣ አንድ ሰው በቫይረሱ በሽታ ምክንያት ከሞተና ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ፣ የቫይረሱ መዛመት ከጨመረ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።
በሀገሪቱ ባለፈው ቅዳሜ 11 የኮቪድ -19 በሽተኞች ተገኝተዋል፤ ለመጀመርያ ጊዜም አንድ ሰው በቫይረሱ ሞቷል። ይህ የሆነው በሀገሪቱ የኮሮናቫይረስ መዛመትን ተቆጣጥረናል የሚል ስሜት ባደረበት ወቅትመሆኑ ተዘግቧል።
ሩዋንዳ የቫይረሱን መዛመት ለመገደብ ስትል፣ በመዲናዋ ኪጋሊም ሆነ፣ በክፍለ-ሀገራት መካከል፣ የመኪኖች እንቅስቃሴመገደቡን ቀጥላለች።በሀገሪቱም 370 የኮቪድ በሽተኞች እንዳሉ ታውቋል።