በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ


አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5798 የላብራቶሪ ምርመራ 169 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1805 ደርሷል ይላል፣ የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ከ1 ዓመት እስከ 78 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች 111 ወንዶች እና 58 ሴቶች ናቸው። 168 ኢትዮጵያውያን እና 1 የአሜሪካን ሃገር ዜጋ ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 138 ከአዲስ አበባ፣ 4 ከትግራይ፣ 4 ከደቡብ፣ 11 ከኦሮሚያ፣ 6 ከአማራ፣ 1 ከሃረሪ እና 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል ናቸው ሲል፣ የጤና ሚኒስተር በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡

አስተያየቶችን ይዩ (1)

XS
SM
MD
LG