በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ


በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከተደረጉ፣ 5141 የላብራቶሪ ምርመራዎች ውስጥ አንድ መቶ ሃምሳ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,636 ደርሷ ይላል የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርመረጃ፡፡

ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰቦች፣ ከ3 ዓመት እስከ 72 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ 94 ወንዶች እና 56 ሴቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 147ቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 3ቱ የውጭ ሃገር ዜጎች ናቸው፡፡ 123 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 1 ከአፋር፣ 2 ከትግራይ፣ 3 ከደቡብ ክልል፣ 2 ከኦሮሚያ፣ 13 ከአማራ እና 6 ሰዎች ከሶማሌ ክልል መሆናቸውን፣ የጤና ሚኒስተር በፌስቡክ ገጹ ላይ፣ በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡

አስተያየቶችን ይዩ (1)

XS
SM
MD
LG