በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዓለም


ፎቶ ፋይል፦ የወል መቃብር /ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ/
ፎቶ ፋይል፦ የወል መቃብር /ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪካ/

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ ከሚቀርቡት በኮሮናቫይረስ የተያዙና በሞት የተለዩት ስዎች አሀዞች ጀርባ፣ ትልቅ ስቃይና ሃዘን አለ አሉ።

በዓለማቀፍ ደረጃ ወደ 20ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች፣ በኮሮናቫይረስ እንደተያዙ 750,000 የሚሆኑት ደግሞ እንደሞቱ ተረጋግጧል።

ዶ/ርቴድሮስ ጄኔቫ ላይ፣ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ይህ ለዓለም ህዝብ ከባድ ሁኔታ ቢሆንም፣ በማንኛዋም ሃገር ቢሆን የተስፋ ምልክት መፈንጠቁ አይቀርም፤ የወረርሽኙን ይዘት ለመለውጥ፣ ምን ጊዜም ቢሆን የዘገየ ሊሆን አይችልም ብለዋል።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በበረታባቸው ሃገሮች ሳይቀር፣ ሁሉም መንግሥታትና ማኅበረሰቦች፣ ምላሽ በማስጠት መቆጣጠር ይቻላል” በማለት አስረድተዋል። የታመሙትን በጊዜ ተከታትሎ በማግኘት፣ የተነካኩትን ደርሶ በማወቅ፣ ለታመሙት በቂ ህክማና በማድረግ፣ የአካል ርቀትን በመጠበቅ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማደረግ፣ ሁሌም ቢሆን እጅን በመታጠብና ከሌሎች ርቆና ፌትን አዙሮ በመሳል፣ የወረርሽኙን መዛመት ለመቆጣጠር እንደሚቻል፣ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ጠቁመዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ደቡብ ኮርያ፣ ስፓኝ፣ ኢጣልያንና ብሪታንያን በምሳሌነት ጠቅሰዋል። እነዚህ ሃገሮች ከባድ የወረርሽኙ መዛመት ገጥሟቸው ነበር፤ ነገር ግን ሊቆጣጠሩት ችለዋል ሲሉ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG