ዋሺንግተን ዲሲ —
ሜክሲኮ ውስጥ በቫይረሱ የሞቱት ሰዎች ብዛት፣ 35,006 መድረሱን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ትናንት አስታውቋል። በዓለም ደርጃ አራተኛውምን ቦታ ይዛለችል። ሰዎች የአካል ርቀትን እንዲጠብቁ፣ የአፍና የአፍንጫ ጭምብል እንዲያደጉና እጅ መጣጠቡን እንዲቀጥሉ መክሯል።
በዩናይትድ ስቴስ ትናንት ከ60,000 በላይ አዲስ የቫይረሱ በሽተኞች መኖራቸው ታውቋል። ፍሎሪዳ፣ ቴክሳስ፣ ሉዊዝያናና አሪዞና በሚገኙባቸው በርካታ ክፍላተ-ግዛት፣ የወረሽኙ መጠን እየጨመረ ሄዷል።
ስፔን በቫይረሱ መዛመት ክፉኛ ከተጎዱት የዓለም ሃገሮች አንዷ ስትሆን፣
ባለፈው ወር የመንቀሳቀስ ገደቡን ማላላት ጀመረች። ነገር ግን አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ፣ አንዳንድ የአካባቢ ባለሥልጣኖች፣ እንቅሳቃሴን ወደ መገደብ እየተመለሱ መሆናቸው ታውቋል።
ከአፍሪካ የበዙ የኮቪድ-19 ቫይረስ በሽተኞች ባሏት ደቡብ አፍሪካ፣ የቫይረሱ በሽተኞች ብዛት እየጨመረ በመሄዱ፣ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ትናንት የአልኮል መጠጥ እንዳይሸጥ በድጋሚ አግደዋል። አዲስ የሰዓት እላፊ ገደብም ደንግገዋል።