በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19


የኮቪድ-19 ታማሚ በሂዩስተን ቴክሳስ ሆስፒታል
የኮቪድ-19 ታማሚ በሂዩስተን ቴክሳስ ሆስፒታል

በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 የተጋለጡት ሰዎች ብዛት ከ12ሚሊዮን ማለፉን የዩናይትድ ስቴትሱ የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የወርርሽኙ መረጃ ማዕከል ያመለክታል፤ ከዚህ ውስጥ ከ3ሚሊዮን የሚበልጠውን የያዘችው ዩናይትድ ስቴትስ ስትሆን ትናንት ሃሙስ ብቻ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከሥድሳ አራት ሽህ የሚበልጡ ሰዎች በምርመራ ተገኝተዋል።

በወርርሽኙ በከባዱ የተጠቁት የምዕራብ እና ደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ ግዛቶች አሪዞና፣ ካሊፎርኒያ ቴክሳስ ፍሎሪዳን ጨመሮ ሆስፒታሎቻቸው የጽኑ ህሙማን ክፍሎች እየተጨናነቁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የሃገሪቱ ከፍተኛው የተላላፊ በሽታዎች ኤክስፐርቱ ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የክፍለ ግዛት አስተዳዳሪዎች እንቅስቃሴዎችን የመክፈት ዕቅዶቻቸውን እንዲያዘገዩ ተማጽነዋል።

ሃገሪቱ የቫይረሱን መዛመት መግታት እስካሁን ባይሆንላትም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ መወትወታቸውን ቀጥለዋል።

XS
SM
MD
LG