በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዓለም ዙሪያ


አውስትራሊያ ውስጥ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመቆጣጠር የእንቅስቃሴ ክልከላዎች ያወጁ ትልልቅ ከተሞች ቁጥር እየጨመረ ነው። አሊስ ስፕሪንግስ የተባለችው ከተማ ከትናን ማክሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት ሰዉ ከቤቱ እንዳይወጣ መመሪያ ተሰጥቷል።

ኢንዶኔዥያ ውስጥ በገባው ዴልታ በተባለው የኮሮናቫይረስ ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን የተናጋረው የሀገሪቱ ቀይ መስቀል በዚህ አያያዝ ሃገሪቱ ወደከባድ ቀውስ አፋፍ እያመራች ነች ሲል አስጠነቀቀ።

ሩስያ በዛሬው ዕለት ብቻ 669 ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸውን ማጣታቸውን አስታወቀች። እስካሁን በአንድ ቀን ከተመዘገበው ሁሉ ትልቁ ቁጥር መሆኑን አመልክታለች።

በዓለም ዙሪያ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለው ሲጀምር ህንድ ላይ የተከሰተው ዴልታ የተባለው የኮሮናቫይረስ ዝሪያ ከሰማኒያ በሚበልጡ ሃገሮች ታይቷል፥ በዚህም ምክንያት የዓለም የጤና ድርጅት የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቱን ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎችም ጭምር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀማቸውን እና ሌሎቹንም የጥንቃቄ መንገዶች መተግብራቸውን እንዲቀጥሉ እያሳሰበ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ ሎስ አንጀለስ ከተማ ባለሥልጣናትም ነዋሪዎች ዝግ ስፍራዎች ውስጥ ከሆኑ ማስክ እንዲጠቀሙ መክረዋል።

በዓለም ዙሪያ ባሁኑ ወቅት በኮሮናቫይረስ የተያዘው ሰው ቁጥር 182 ሚሊዮን ተቃርቧል። ለህልፈት የተዳረጉትም ቀጥር ወደ አራት ሚሊዮን እየተቃረበ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ጃንስ ሃፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ሰንጠረዥ ያሳያል።

ዛሬ የተመድ የንግድ እና የልማት ጉባኤ እንዲሁም የድርጅቱ የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ባወጡት ሪፖርት ኮቪድ-19 ባለፈው የአውሮፓ 2020 በዓለም አቀፍ ቱሪዝም እና ተያያዥ ዘርፎች ላይ የ2 ነጥብ 4ትሪሊዮን ዶላር ኪሳራ አስከትሏል።

በዘርፉ ላይ ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የሰባ ሦሶት ከመቶ ኪሳራ እንዳስከተለ ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG