በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"5 ሚሊዮን ሰዎች የወረቀት ላይ ቁጥሮች አይደሉም" - ተመድ


የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ በኮቪድ-19 የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ5ሚሊዮን በላይ በልጧል መባሉን “ዓለም አቀፍ ሀፍረት ነው” ሲሉ ትናንት ሰኞ በሰጡት መግለጫ ተናገሩ፡፡

ዓለም ለዚህ የበቃው ፍትሃዊ ባልሆነ የክትባት ስርጭት የተነሳ መሆኑንም ዋና ጸሀፊው ተናግረዋል፡፡

ጎተሬዥ “እነዚህ ቁጥሮች (5 ሚሊዮን ሰዎች) ዝምብሎ የወረቀት ላይ ያሉ ቁጥሮች አይደሉም እናቶች አባቶች ናቸው፡፡ ወንድሞችና እህቶች ሴትና ወንድ ልጆች ናቸው፡፡ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች ናቸው፡፡ ድንበር በማይወስነው ምህረት አልባ በሆነው ቫይረሰ ህይወታቸው በአጭር የተቀጨ ናቸው፡፡” ብለዋል፡፡

የጆን ሀፕንኪስ ዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 የመረጃ ማዕከል ትናንት በሰጠው መግለጫ በመላው ዓለም በኮቪድ 19 ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር ከአራት ወራት በፊት 4 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን አሁን ከ5 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ዋና ጸሀፊው የበለጸገው ዓለም ለሦስተኛ ዙር የማጠናከሪያ ክትባት ለመስጠት ሲጀምሩ በመላው አፍሪካ ሙሉውን ክትባት ማግኘት የቻሉት 5 ከመቶ የሚሆኑን ያህል ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG