በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በህንድ


ህንድ ውስጥ በኮቪድ-19 ሳቢያ ዛሬ ሃሙስ ብቻ 6,143 መሞታቸውን አስታወቀች። ይህም በዓለም ዙሪያ እስካሁን በአንድ ቀን ከተመዘገቡት ከፍተኛው መሆኑ ተገልጿል።

ከትላልቆቹ እና በድህነት ውስጥ ከሚገኙ የህንድ ክፍላተ ሃገር አንዱ የሆነው ምስራቃዊው ቢሃር ክፍለ ሃገር ትናንት ረቡዕ አውጥቶት የነበረውን በኮቪድ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 5,500 የነበረ ሲሆን በከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደገና ከልሶ 9,500 መሆናቸውን ዘግቧል።

በርካታ የጉዳዩ አዋቂዎች በሀገሪቱ በተስፋፋው ኮቪድ-19 ህይወታቸውን የሚያጡት ሰዎች ቁጥር በይፋ እየተነገረ ካለው እንደሚበልጥ ሲናገሩ ቆይተዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ጃንስ ሃፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል መሰረት ህንድ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ብዛት 29 ነጥብ 1 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን 355,705 ስዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

ከህንድ የሚበልጥ ቁጥር ያላት ዩናይትድ ስቴትስ ብቻ ስትሆን ለቫይረሱ የተጋለጡት ሰዎች 33 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሲሆን ለህልፈት የተዳረጉት ደግሞ 598,766 መድረሱን መረጃው ያሳያል።

በሌላ በኩል ከአስትራ ዜኔካው የኮቪድ-19 ክትባት በተያያዘ የሚከሰት የደም መፍሰስ እክል በመጠኑ ከፍ ያለ ሊያጋጥም እንደሚችል ኔቸር ሜዲሲን መጽሄት ላይ የታተመ አንድ አዲስ ጥናት ጠቆመ።

ጉዳዩን የተከታተሉ ተመራማሪዎች ስኮትላንድ ውስጥ ክትባቱን የወሰዱ አንዳንድ ሰዎች “ኢሚዩን ትሮምቦሳይቶፔኒክ ፑርፑራ” /አይቲፒ/ የሚባለው በአንዳንዶች ላይ ላይ የሚታይ የደም መዝጎን፣ በአንዳንድ ሰዎችን ደግሞ ለከባድ የደም መፍሰስ የሚዳርግ ሁኔታ ሊያጋልጥ እንደሚችል እንደደረሱበት ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG