በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማረሚያ ቤት የፍርድ ቤትን ትእዛዝ እየፈጸመ እንዳልኾነ የሽብር ተከሳሾች አመለከቱ


ማረሚያ ቤት የፍርድ ቤትን ትእዛዝ እየፈጸመ እንዳልኾነ የሽብር ተከሳሾች አመለከቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:45 0:00

ማረሚያ ቤት የፍርድ ቤትን ትእዛዝ እየፈጸመ እንዳልኾነ የሽብር ተከሳሾች አመለከቱ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሕገ መንግሥት እና ሽብር ወንጀሎች ችሎት፣ ከመደበኛው የጊዜ ቀጠሮ በተለየ፣ የሽብር ተከሳሾችን የሰብአዊ መብቶች አቤቱታን ተመልክቶ፣ ለማረሚያ ቤቶች በድጋሚ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

ከአማራ ክልል ጸጥታዊ ቀውስ ጋራ በተያያዘ በሽብር የተከሰሱት እነአቶ ዮሐንስ ቧያለው እና እነ ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ፥ “በቤተሰብ የምግብ አቅርቦት እና ጥየቃ ላይ በማረሚያ ቤት የተጣለው ገደብ እንዲነሣና ሌሎችም የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩልን የተሰጠው ትእዛዝ አልተከበረም፤” ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች፣ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መሠረት ዛሬ ዐርብ ችሎት ቀርበው በአቤቱታው ላይ ማብራሪያ መስጠታቸውንና ችሎቱም ትዕዛዙ በምልአት እንዲከበር በድጋሚ ማዘዙን፣ ከተከሳሽ ጠበቆች አንዱ ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ ለአሜሪካ ድምፅ አብራርተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG