በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእነአቶ ጃዋር መሃመድ ጉዳይና በዋስ የተለቀቁ ጋዜጠኞች


አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።

ችሎቱ አቃቤ ሕግ በከፈተው የቅድመ ምርመራ መዝገብ ላይ የምስክሮች ቃል እንዲሰማ ለነሃሴ 4/2012 ዓ.ም መቅጠሩን የህግ አቶ ከድር ቡሎ ገልፀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳ፣ ከንያዊው ጋዜጠኛ ያሲን ጁማን እና ዘጠኝ ሰዎች በዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ትናንት ወስኗል።

ችሎቱ በጪብሳ አብዱልከሪም እና በጁምባ ያሲን መዝገብ የተከሰሱ ሰዎች በዋስ ትዕዛዝ ቢያስተላልፍም የታሳሪ ቤተሰቦች የዋስትና ማስከበሪያ ክፍያ ከፈፀሙ በኋላ ለተጨማሪ ምርመራ እንደሚፈልጋቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደነገራቸው የቤተሰብ አባላት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የእነአቶ ጃዋር መሃመድ ጉዳይና በዋስ የተለቀቁ ጋዜጠኞች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:17 0:00


XS
SM
MD
LG