በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዱባዩ ገዥ ለፈጸሙት ፍቺ 730ሚሊዮን ዶላር ተፈረደባቸው


ፎቶ ፋይል፦ ልዕልት ሃያ ቢንት አል ሁሴን
ፎቶ ፋይል፦ ልዕልት ሃያ ቢንት አል ሁሴን

እንግሊዝ ለንደን ውስጥ የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት በተባበሩት አረብ ኤምሬት ምክትል ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህ መሃመድ ቢን ራሺድ አልማክቶም ለፈጸሙት የጋብቻ ፍቺ የ730ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍሉ የወሰነባቸው መሆኑን ተሰማ፡፡

ውሳኔው የተለለፈባቸው ባላፈው ሀሙስ ሲሆን የዱባይ ገዥ ጭምር የሆኑት ሼህ መሃመድ ለልዕልት ሃያ ቢንት አል ሁሴንና ለልጆቻቸው ዘላቂ ህይወት የሚሆን የ730 ሚሊዮን ዶላሩን እንዲከፍሉ የተወሰነባቸው መሆኑን ተመልክቷል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤት ለደህንነታቸው ሲሉ ወደ እንግሊዝ የተሰደዱት እኤአ በ2019 መሆኑም በሮይተርስና የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG