በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተፈረደባቸዉ የሙስሊም ችግሮች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ጠበቃ፣ ይግባኝ እንጠይቃለን አሉ

በሽብር ወንጀል ተከሰዉ ትላንት ቅጣት የተጣለባቸዉ የሙስልም ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጠበቃ፣ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃለምልልስ የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ግራ አጋብቶናል ይላሉ።

በሽብር ወንጀል ተከሰዉ ትላንት ቅጣት የተጣለባቸዉ የሙስልም ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጠበቃ፣ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃለምልልስ የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ግራ አጋብቶናል ይላሉ።

የኮሚቴዉን አባላት ጉዳይ ከጅምሩ ከተከታተሉት ጠበቆች አንዱ የሆኑት አቶ መሀመድ አብደላ ያቀረብናቸዉ ማስረጃዎች ደንበኞቻችን ከመከላከል በላይ የሚያስረዱ ሆኖ ሳለ፣ ፍርድ ቤቱ ዉድቅ ማድረጉ አግባብነት የለዉም ይግብኝ እንጠይቃለን ብለዋል።

በነ አቶ አቡበከር አህመድ መሃመድ የክስ መዝገብ በአቃቤ ሕግ የተከሰሱትና እስከ ሃያ ዓመት እስራት ቅጣት የተፈረደባቸዉ አስራ ስምንት ግለሰቦች አብዛኞቹ የሃይማኖት መምህራን እንደሆኑና የገለጹት የህግ ባለሙያ መሃመድ አብደላ፥ በሽብር ወንጀል ያለመሳተፋቸዉን ለማስረዳት አያሌ የሰነድ፣ የሰዉና፣ የድምጽ ከምስል ማስረዳዎች ለፍርድ ቤቱ ማቅረባቸዉን ያናገራሉ። ይሁንና ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎቹ በምን ምክንያት ዉድቅ እንደተደረጉ ሳያስረዳ ደንበኞቻችንን ጥፋተኞች ብሎ ወሰኖአል ብለዋል።

ፍርድ ቤቱ ደንበኞቻቸዉ በሃይማኖት ጉዳይ እንዲከላከሉ በማዘዙም የሃይማኖት ምሁራንን በምስክርነት አቅርበዉ ተቀባይነት እንዳጡ በመጨረሻ ግን የሃይማኖት ጽንጸ ሃሳብ መሰረት ተደርጎ ጥፋተኞች መባላቸዉን በዝርዝር አስረድተዋል።

ዝርዝሩን መለስካቸዉ አመሃ ከላከዉ ሪፓርት ያድምጡ።

የተፈረደባቸዉ የሙስሊም ችግሮች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ጠበቃ፣ ይግባኝ እንጠይቃለን አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:06 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG