በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ሳርኮዚ አንድ ዓመት ተፈረደባቸው


የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኒኮለስ ሳሮኮዚ
የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኒኮለስ ሳሮኮዚ

የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኒኮለስ ሳሮኮዚ እኤአ በ2012 በተደረገው ምርጫ ዘመቻ ወቅት በፋይናንስ ማጭበርበር ጥፋተኛ ሆኖ ያገኛቸው በመሆኑ አንድ የፈረንሳይ ፍርድ ቤት፣ የአንድ ዓመት እስር ፈርዶባቸዋል፡፡

አቃቢ ህግ፣ ሳርኮዚ ተቀናቃኛቸው ፍራንሷስ ሆላንድ ባሸነፉበት ምርጫ ወቅት በፈረንሳይ ህግ በምርጫ ወቅት ከተፈቀደው የገንዘብ መጠን በላይ እጥፍ ገንዘብ አውጥተዋል ብሏል፡፡

ፈረንሳይን እኤአ ከ2007 እስከ 2012 የመሩት ሳርኮዚ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ጠበቃቸውም ይግባኝ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል፡፡

ባላፈው መጋቢት በሌላ የሙስና ወንጀል የተፈረደባቸው ሳርኮዚ፣ በሶስት ዓመት ጽኑ እስራትና የሁለት ዓመት እግድ ተፈርዶባቸው ጉዳያቸው በይግባኝ እየታየ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG