በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአቪዬሸን አሰራርን በመጣስ የተጠረጠሩ 6 ሰዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ


የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት

ባለፈው ሐሙስ ነሐሴ 16 ቀን ከአዲስ አበባ መቀሌ ጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በመፍጠር የተጠረጠሩ ስድስት ተከሳሾች፣ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ቀርበዋል።

የአቪዬሸን አሰራርን በመጣስ የተጠረጠሩ 6 ሰዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:14 0:00

ከተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች አንዷ ጀሚላ መስፍን ለአሜሪካ ድምጽ እንደገለፁት፣ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን የዋስትና ጥያቄ ባለመቀበል፣ የፌደራል ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።

የፌዴሬል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን "ተጠርጣሪዎቹ የአቪዬሽንን የአሰራር ሕግ ከመጣስ ባለፈ በሽብር ወንጀልም ምርመራ ስለጀመርኩ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ይደረግ" በማለት መከራከሪያ ማቅረቡንም ጠበቃዋ አመልክተዋል።

የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው፣ተጠርጣሪዎቹ የፈጸሙት አነስተኛ ጥሰት በሽብር አዋጁ የሚታይ አይደለም በማለት ተከራክረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG