በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካ ቀንድን ከረሃብ ለመታደግ ተጨማሪ ገንዘብ ቃል ተገባ


የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

በአፍሪካ ቀንድ ሥላለው ድርቅና እያንዣበበ ስላለው የጠኔ አደጋ በማስጠንቀቅ ላይ ያሉ ሃገራት በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ተጨማሪ ዕርዳታ ቃል ገብተዋል።

ከአርባ ዓመታት ወዲህ የከፋ ድርቅ በገጠመው የአፍሪካ ቀንድ፣ ዝናቡ ለአምስተኛ ግዜ ላይመጣ ይችላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው የአየር ትንበያ ባለሙያዎች በመግለጽ ላይ ናቸው።

ሶማሊያ በከፊል በሚቀጥሉት ወራት በቸነፈር ትመታለች ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርት ያስጠነቅቃል። የተጎጂዎች ቁጥር ግምት ከአስር ዓመታት በፊት ከነበረው ቸነፈር የከፋ እንደሚሆን ይጠበቃል። በእአአ 2011 በተከሰተው በዚሁ ቸነፈር ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሶማሊያ አልቀዋል። ከነዚህ ውስጥ ግማሾቹ ህፃናት ናቸው።

“አሁን ወደ ተግባራዊ ሥራ የመግቢያ ሠዓት ነው” ብለዋል የድርቅ ጉዳይን በተመለከተ የተመድ የሶማሊያ መልዕክተኛ የሆኑት አብድራህማን ዋርሳሜ ትናንት ረቡዕ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር። የዓለም መሪዎች አብዝተው እንዲለግሱም ጥሪ አድርገዋል።

የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በአፍሪካ ቀንድ ሰዎች “ከሰብዓዊ ዕልቂት ጋር ተፋጠዋል” ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት ኃላፊ የሆኑት ሳማንታ ፓወር፣ ዋሽንግተን ተጨማሪ 151 ሚሊዮን ዶላር ለሶማሊያ እንደምትለግስ አስታውቀዋል።

ጣልያን፣ እንግሊዝና ኳታርም ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚሰጡ ትናንት ረቡዕ በነበረው የተመድ ስብሰባ ወቅት አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG