በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የአማራ ክልል መሬቶች ጉዳይ እልባት ሳያገኝ ህወሓት ምርጫ ማካሄድ አይችልም" የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴና አብን


የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በግዳጅ ወደ ትግራይ የተካለሉ ናቸው ያሏቸው የአማራ ክልል መሬቶች ጉዳይ እልባት ሳያገኝ ህወሓት ምርጫ ማካሄድ አይችልም ሲሉ ተቃውሟቸውን ገለፁ።

ምርጫ ቦርድ የህወሓትን በትግራይ ክልል ምርጫ የማካሄድ ኢ- ሕገመንግሥታዊ ውሳኔ ውድቅ ማድረጉን እንደሚደግፉት ተናግረዋል።

ተቃውሟቸውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደሚያቀርቡም አስታውቀዋል። ሁለቱ የፌደራል ምክር ቤቶች በኮቪድ-19 ምክንያት የኢትዮጵያ ምርጫ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ መወሰናቸው ይታወሳል። ይህን ውሳኔ ያልተቀበለው የትግራይ ክልል ምክር ቤት በበኩሉ ትግራይ ምርጫውን እንድታደርግ ውሳኔ ማሳለፉ አይዘነጋም። በጉዳዩ ዙሪያ ለአሜሪካ ድምፅ ምላሽ የሰጡት የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሊያ ታደሰ “ለወልቃይትና ለራያ ሕዝቦች እናውቅልሃለን የሚሉ ኃይሎች ሃሳብ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም” ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።


XS
SM
MD
LG