በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም የጸረ ሙስና ትግሉ ቆሟል ኮቪድም አልረዳውም ተባለ


በዓለም የጸረ ሙስና አካል በተደረገ ጥናት አብዛኞቹ አገሮች ባላፉት አስርት ዓመታት ሙስናን ለመቀነስ ደረጃቸውን ለማስተካከል ያደረጉት ጥረት እጅግ አነስተኛ ወይም ጨርሶ ምንም ለውጥ ያላመጣ መሆኑን አመለከተ፡፡

ባላሥልጣናት ኮቪድ-19 አስመለከቶ ስለሚያደርጓቸው ነገሮች ያላቸው ተጠያቂነትና ግልጽነት በብዙ ቦታዎች ዝቅተኛ መሆኑን ጥናቱ አስታውቋል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሙስና ላይ የሚደረገው ክትትል እንዲላላና አስተዋጽኦ ማድረጉን ጥናቱ አመልክቷል፡፡

የህዝብና የመንግሥት ተቋማት ሙስን እና ስለሙስና ያለውን አመለካከት የሚለካው ተቋም፣ እኤአ በ2021 ባወጣው ዓለም አቀፍ ግልጽነትና የሙስና አማላካች ጠቋሚ መረጃ እንዳመለከተው ሙስና በዓለም እየጨመረ መጥቷል፡፡

ይህ ደግሞ በደካሞቹ አገሮች ብቻ ሳይሆን የመንግስትና ህዝባዊ ተቋማትን መከታተያና መቆጣጠሪያ ተቋማት ባላቸው የደረጁ አገሮችም ጭምር የሚታይ መሆኑን ጥናቱ አስታውቋል፡፡

አንጻራዊ በመሆነ መልኩ ከሙስና የጸዱ አገሮች ናቸው ተብሎ እስከ አንድ መቶ ድረስ በደረጃ ከተቀመጡ አገሮች መካከል ዴንማርክ ኒውዘላንድ እና ፊላንድ በመጀመሪያ ደረጃ የተቀመጡ ሆነዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ከነበረችበት 25ኛ ወደ 27ኛ ደረጃ መውረዷ ተመልክቷል፡፡

ደቡብ ሱዳን፣ ሶማልያና የመን፣ የመጨረሻዎቹን ዝቅተኛ ሶስት ደረጃዎች ተመድበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG