በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በማዕከላዊና ደቡባዊ አሜሪካ


ፎቶ ፋይል፦ የብራዚል ከተማ ማናውስ ውስጥ የሚገኝ ሆስፒታል
ፎቶ ፋይል፦ የብራዚል ከተማ ማናውስ ውስጥ የሚገኝ ሆስፒታል

የዓለም የጤና ድርጅት፣ ማዕከላዊና ደቡባዊ አሜሪካ፣ ኮሮናቫይረስ የሚዛመትባቸው ቀጠናዎች እየሆኑ ነው ሲል፣ ትናንት ሰኞ አስታውቋል።

የቫይረሱ መዛመት እንደበረታባቸው ያስታወቁት የአሜሪካ ሀገሮች ብራዚል፣ ኮሎምቢያ፣ ፔሩ፣ ቺሊ፣ ሜክሲኮና ቦሊቭያ መሆናቸውን፣ የዓለም የጤና ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ፕሮግራም ዋና ሥራ አስኪያጅማይክ ራያን ጠቁመዋል።

ሜክሲኮ ውስጥ ከ10ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ፣ ከ93ሺህ በላይ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች መኖሮቸውን የሜክስኮ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል። ነገር ግን ብዛቱ ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል፣ የሃገሪቱ ባለሥልጣኖች ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG