በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የአፍሪካ ሀገሮች ዝግጅት


ኮሮናቫይረስ አፍሪካም ሊገባ ይችላል የሚለውን የባለሙያዎች ዕምነትን መስረት በማድረግ የአፍሪካ ሀገሮች እየተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የአፍሪካ ሀገሮች ከቻይና ጋር ያላቸው የኢኮኖሚ ግንኙነት እያደገና በቻይናና በአፍሪካ ሀገሮች መካከል የሚደረገው የሰዎች ዝውውርም እየጨመረ በመሆኑ የአፍሪካ ሀገሮች የሚታመሙትን ለማከምና ለይተው ለማስቀመጥ መዘጋጀት አለባቸው ይላሉ የጤና ጥበቅ ባለሙያዎች።

በውሀን ከተማ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሲከታተሉ ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ሦስት ኢትዮጵያውያንንና አንድ ቻይናዊ ተማሪን ኳራንቲን ውስጥ ማስገባትዋን ወይም ከሌሎች ጋር እንዳይገኙ መለየትዋን ትላንት ገልጻለች።

ተማሪዎቹ ትኩረት የተደረገብቸው ለጥንቃቄ ሲባል በቦሌ አይውፕላን ማረፍያ ላይ ሲመረመሩ የጉሮሮ መከርከርንና ሳልን ያካተተ የህምም ስሜት ስለነበረባቸው መሆኑ ተግልጿል።

የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሙኒር ካሳ ኢትዮጵያ ለበሽታው መከላከል ዝግጁ መሆንዋን ገልጸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG