በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገው በረራ


አቶ ተወልደ ገብረ-መርያም
አቶ ተወልደ ገብረ-መርያም

ቻይና ውስጥ በተዛመተው የኮሮናቫይረስ በሽታ ምክንያት ዓለምአቀፍ የአውሮፕላን በረራዎች ወደ ቻይና መብረሩን ባቆሙበት በአሁኑ ወቅት ትልቁ የአፍሪካ የአየር በረራ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አላቆምም ማለቱ ተዘግቧል።

አየር መንገዱ በራራውን እንዲያቆም ጫና እየተደርገበት ቢሆንም የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገብረ-መርያም የአውሮፕላን በረራ ማቆም የቫይረሱን መዛመት የሚገታ መሆኑን የሚያሳይ ማሰረጃ የለም ማለታቸው ተጠቅሷል። ከቻይና ባለሥጣኖች ጋር በመተባበር ምርመራ ማድረግ ይበጃል ብለዋል።

“ቻይናን ማግለል አይኖርብንም። የቻይና ተሳፋሪዎችን ማራቅ አይገባም። ማድረግ ያለብን በዓለምቀፍ የጤና ድርጅት መመሪያ መሰረት ለመንገደኞቹ የጤና ምርመራ ማደረግ ነው” ብለዋል አቶ ተወልደ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በተዘገበው መሰረት።

በያዝነው ሳምንት 47,167 የሚሆኑ ተሳፋሪዎች በኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ተመርምረዋል። 1,607 የሚሆኑት ከቻይና የተጓዙ ናቸው። ጥቂቶች የቫይረሱ ስሜት ስለታየባቸው በተወሰነ ቦታ እንዲቆዩ ተደርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አምስት የቻይና መዳረሻዎች በሳምንት 35 በረራዎች ያደርጋል ታብሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG