በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲስ የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍ ማለቱ ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ የኮቪድ ክትባት አገልግሎት በሎስ አንጀለስ ሲቪዬስ ፋርማሲ
ፎቶ ፋይል፦ የኮቪድ ክትባት አገልግሎት በሎስ አንጀለስ ሲቪዬስ ፋርማሲ

በዓለም ዙሪያ የአዲስ የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር ከሰባት ሳምንታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍ ማለቱን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።

የቫይረሱ ስርጭት እንደገና ከበድ ባለ መጠን ሊያሻቅብ እንደሚችልም ባለሥልጣናቱ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የድርጅቱ የኮቪዲ-19 ቴክኒካዊ ክፍል ኃላፊዋ ማሪያ ቫን ኸርኾቭ በጄኔቫ የድርጅቱ ዋና ጽህፈት ቤት ባደረጉት ገለፃ፣ ቫይረሱ ዕድሉን ከሰጠነው እንደገና ሊያንሰራራ እንደሚችል አውቀን መጠንቀቅ ይገባናል ብለዋል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው በአራት የዓለም አካባቢዎች በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በደቡብ ምስራቅ እስያ የቫይረሱ አዲስ ተያዦች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑ ገልጸዋል።

“ይህ ቢያሳዝነንም አያስገርመንም” ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ ለቫይረሱ ስርጭት ማሻቀብ አንዱ ምክንያት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተወስዱ ርምጃዎች መርገባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።

XS
SM
MD
LG