በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስካሁን ስምምነት ያልተደረሰበት 28ኛው አየርን ንብረት ጉባዔ የመጨረሻ ቀኑን ይዟል


የኮፕ 28 ዳይሬክተር ጀነራል ማጂድ አል-ሱዋኢዲ
የኮፕ 28 ዳይሬክተር ጀነራል ማጂድ አል-ሱዋኢዲ

ዓለምን እየጎዳ ላለው ሙቀት ተጠያቂ የሆነውን ከከርሰ ምድር የሚወጣ ኃይልን መጠቀም እንዲቆም በሚፈልጉ እና በማይፈጉ ሀገራት መካከል የሚካሄደው ውይይት ያለስምምነት መቀጠሉ በአየር ንብረት ጉባዔው ላይ የተጣለውን ተስፋ አመናምኗል።

ለሁለት ሳምንታት የተለያዩ ንግግሮችን፣ ተቃውሞዎችን እንድ ድርድሮችን ሲያስተናገድ በቆየው፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚካሄደው 28ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባዔ፣ ከከርሰ ምድር የሚወጡ የድንጋይ ከሰል፣ ዘይት እና ጋዞችን በፍጥነት መጠቀም ማቆም የሚያስችል የውሳኔ ሀሳብ እንዲያሳልፍ ተጠብቆ ነበር። ሆኖም ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡ ያቀረበው 'ምክንያታዊ፣ ስርዓት ባለው እና ፍትሃዊ' በሆነ መልኩ መጠቀምን የሚያበረታታ መሆኑ፣ በርካታ ሀገራትን አስቆጥቷል።

የኮፕ 28 ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት ማጂድ አል-ሱዋኢዲ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ሰኞ እለት ይፋ የተደረገው ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ሀገራት በጉዳዩ ላይ ማውራት እንዲጀምሩ እና እነሱ ቀይ መስመር ብለው የሚያስቀምጧቸውን ጉዳዮች ለይተው እንዲያቀርቡ የሚያነሳሳ ነው ሲሉ ተከላክለዋል።

ታዳጊ ሀገራትን ወክለው በድርድሩ ላይ የተሳተፉ እና ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ ተደራዳሪ በበኩላቸው ከከርሰ ምድር የሚወጡ ኃይሎችን በደረጃ መጠቀም ማቆም በውሳኔ ሀሳቡ ላይ እንደማይካተት ገልፀዋል።

"የከርሰ ምድር ኃይልን አስመልክቶ የምንጠቀመው ቋንቋ ትክክለኛ መሆን አለበት" ያሉት አል-ሱዋኢዲ "ሁሉንም ያማከለ ስምምነት ማግኘት የምንችልበትንም መንገድ ማሰብ አስፈላጊ ነው። አንዳንዶች በደረጃ እንዲቆም ይፈልጋሉ። አንዳንዶች ደግሞ በደረጃ እንዲቀንስ ይፈልጋሉ" ብለዋል።

ዋናው ነገር ሁለቱን ፍላጎቶች ማስማማት መቻል መሆኑንንም አስምረውበታል።

እንደ ሳዑዲ አረብያ ያሉ ሀገራት የከርሰ ምድር ኃይልን ቀስ በቀስ መጠቀም ማቆም የሚለውን ቋንቋ የማይቀበሉ ሲሆን፣ የአውሮፓ እና ትናንሽ ደሰቶችን የመሳሰሉ ሀገራት ደግሞ ይህንን ሀሳብ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ማድረግ ተቀባይነት የለውም ሲሉ ይከራከራሉ።

የአየር ንብረት ተሟጋቾች በበኩላቸው እንደ ሳዑዲ አረብያ ያሉ ዋና የነዳጅ አምራች አገሮች የከርሰ ምድር ሀብትን መጠቀም ማቆም መቃወማቸው፣ የሚጠበቀውን የውሳኔ ሀሳብ እንዳላላው በመግለፅ፣ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG