በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ የአፍሪካ አገሮች ጥያቄ አቀረቡ


ግብፅ ሻርም ኤል ሼኽ በተካሄደው የCOP27 የየተባበሩት መንግሥታት ጉባዔ፣ ላይ በተደረገ ተቃውሞ አክቲቪስቶች ተሳትፈዋል።
ግብፅ ሻርም ኤል ሼኽ በተካሄደው የCOP27 የየተባበሩት መንግሥታት ጉባዔ፣ ላይ በተደረገ ተቃውሞ አክቲቪስቶች ተሳትፈዋል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት ግብፅ ላይ በተጀመረው በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ባተኮረው የተባበሩት መንግሥታት ጉባዔ፣

"በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ጉዳት ለሚደርስባቸው በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የገንዘብ ድጋፍ መደረግ አለበት" በሚል በአፍሪካ እና በምዕራባውያን ሃገሮች መካከል በተደረገው ክርክር ቻይና ጠንከር ያለ ሚና እንደነበራት ተገለጠ።

በያዝነው ዓመት ብቻ በደቡብ አፍሪካ የደረሰውን አውዳሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና በአፍሪካ ቀንድ ላለፉት በርካታ ዓመታት ታይቶ የማያውቅ የተባለ ድርቅ ጨምሮ አፍሪካ በአየር ንብረት መዛባት የተነሳ ብርቱ ጉዳት ያደረሱ ፈተናዎችን አስተናግዳለች።

በCOP27 የተሳተፉት የአፍሪካ አገሮች የበለፀጉት አገሮች ካሳ እንዲከፍሉ እና "ኪሳራ እና ጉዳት" በሚል ከአየር ንብረት ጋር ለተዛመዱ ጉዳዮች ለሚሰበሰብ ገንዘብ እንዲያዋጡ” ሲሉ ብርቱ ግፊት እያደረጉ ነው።

ቻይና፣ ብራዚል፣ ህንድ እና ደቡብ አፍሪካ በጋራ ባወጡት መግለጫ የበለጸጉ አገሮች ራሳቸው በካይ ካርቦን የሚለቀውን የነዳጅ ዘይት እየተጠቀሙ በማደግ ላይ ያሉ አገሮችን ከብክለት የነጻ ዘዴ እንዲከተሉ ይገፋፋሉ” ሲሉ ከሰዋል።

የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮወሪ ሙሴቬኒ በበኩላቸው በማኅበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “የምዕራባውያን ሁለት ለየቅል የሆኑ አሰራሮችን ይከተላሉ” ሲሉ በመክሰስ አንዳንድ የአውሮፓ ሃገሮች የድንጋይ ከሰል ወደማውጣት እየተመለሱ ናቸው ሲሉ ተችተዋል።

XS
SM
MD
LG